Amharic

Amharic Language

ክርስቲያን የሚለው ቃል በሐዲስ ኪዳን ሦስት ጊዜ ተጠቅሶ እናገኝዋለን (የሐዋርያት ሥራ ፲፩፥፳፮፤ የሐዋርያት ሥራ ፳፮፥፳፰፤ ፩ኛ ጴጥሮስ ፬፥፲፮)። የኢየሱስ ተከታዮች ክርስቲያን የሚል ስም በመጀመሪያ በአንጾኪያ ተሰጣቸው (የሐዋሪያት ሥራ ፲፩፥፳፮)፤ ይህም ስም የተሰጣቸው ሥራቸውና ጸባያቸው እንደክርስቶስ ስለነበር ነው። በመጀመሪያ ይህ ስም ያልዳኑት የአነጾኪያ ሰዎች ክርስቲያን የሆኑትን ላይ ለማላገጥ ያወጡላቸው ስም ነበር። ቀትተኛ ተርጉሙም፣ “የክርስቶስ ማኀበር አባል” ወይንም “የክርስቶስ ተከታይ” ማለት ነው።

ሐዋርያው እንድርያስ የስምዖን ጴጥሮስ ወንድም ነበረ። ወንድማማቾቹ እንድርያስና ጴጥሮስ ጌታ ኢየሱስን ለመከተል አንድ ላይ ነው የተጠሩት (ማቴ. 4፥18) ። መጽሐፍ ቅዱስ እንድርያስን ከአሥራ ሁለቱ ሐዋርያት አንዱ አድርጎ ሰይሞታል (ማቴ. 10፥2) ። እንደ ወንድሙ ጴጥሮስ ሁሉ እንድርያስም በገሊላ ባሕር ዓሣ አጥማጅ ነበር። ጴጥሮስና እንድርያስ መኖሪያቸው በገሊላ ሰሜናዊ ምዕራብ ዳርቻ በቤተ ሳይዳ ከተማ ነበር (ዮሐንስ 1 44) (ዮሐ. 12፥21) ።

የሉቃስ ወንጌል የሚጀምረው ስለ ኢየሱስ መወለድ ብስራት በመናገር ነው: የመጥምቁ ዮሐንስ መወለድ፤ ኢየሱስ በግርግም ወደተወለደበት ወደ ቤተልሔም የማርያምና የዮሴፍ ጉዞ፤ እንዲሁም በማርያም በኩል የክርስቶስ የትውልድ ሐረግ። ኢየሱስ ባደባባይ ባስተማራቸው ትምህርቶች ውስጥ ፡ ሰለ ጠፋው አባካኙ ልጅ፣ ስለ ሀብታሙና ስለ አልዓዛር እንዲሁም ስለ ደጉ ሳምራዊ በሚነገሩ ታሪኮች አማካኝነት ፍጹም የሆነ ርኅራኄና ይቅርታ አሳይቷል። ብዙዎች ከሰው ልጆች አቅም በላይ በሆነው በዚህ እውነተኛ ፍቅር ቢያምኑም ሌሎች ግን በተለይም የሃይማኖት መሪዎች የኢየሱስን ትምህርት ሊቀበሉት ስላልቻሉ ይቃወሙት ነበር። የክርስቶስ ተከታዮች የደቀመዝሙርነትን ዋጋ እንዲያስተውሉ ይበረታታሉ። ጠላቶቹ ግን ሞቱን በመስቀል ላይ ይፈልጋሉ። በመጨረሻም ኢየሱስ በይሁዳ ተከድቶ ፍርድ ተበይኖበት ተሰቀለ። መቃብር ግን ሊይዘው አልቻለም! የእርሱ ትንሳኤ የጠፉትን የመፈለግ እና የማዳን አገልግሎቱን መቀጠል አስፈላጊነት ያረጋግጣል።

የኒቂያ ጉባኤ የተካሄደው ከክርስቶስ ልደት በኋላ በሮማ ንጉሠ ነገሥት ቄሣር በፍላቪየስ ቆስጠንጢኖስ ትእዛዝ በ 325 ዓመተ ምህረት ነበር። ኒቂያ የምትገኘው ከቁስጥንጥንያ በስተምሥራቅ በምትገኘው በትንሿ እስያ ነበር ። በኒቂያ ጉባኤ ላይ አፄ ቆስጠንጢኖስ የክርስቶስን አምላክነት በተመለከተ በቤተ ክርስቲያኒቱ ውስጥ ያለውን ግራ መጋባት፣ ውዝግብና አለመስማማት ለማስወገድ በሚል ዓላማ 318 የቤተ ክርስቲያን  ሊቃውንት ጳጳሳትንና ሌሎች መሪዎች የተገኙበትን ጉባኤ መርተዋል። የኒቂያ ጉባኤ የኢየሱስ ክርስቶስን አምላክነት እና ዘላለማዊነት በከፍተኛ ሁኔታ አረጋግጦ በአብ እና በወልድ መካከል ያለውን መተካከል ተቀብሎ አጽንቶታል።