ዘማሪ - ፈቃዱ አማረ
አዝማች
እልል በሉ በአንድነት ዘምሩ ፡
አመስግኑ ለክብሩ ዘምሩለት ፡
እንደ እግዚአብሔር ያለ ማንም የለም በሉ (2)።
በኃጢያት ባርነት ስንኖር ተገዝተን ፡
ከቤቱ ስንርቅ ተእዛዙን አፍርሰን ፡
አይቶ ዝም ላለን ጠላቶቹ ሳለን ፡
ዉለታው ብዙ ነው ፡ ክብር ለሱ ይሁን (2)።
አዝማች - -
እራሱን አዋርዶ እኛን አከበረን ፡
ስጋውና ደሙን ብሉ ጠጡ አለን።
መልካም እረኛ ነው የሚያሳጣን የለም፡
ምስጋና ይድረሰው ለመድኃኒዓለም (2)።
አዝማች - -
ህይወቱን የሰዋ እንደ አምላክ ማን አለ?
ለሰው ልጆች ብሎ በመስቀል የዋለ።
ፍቅሩ ባይለካ ባያልቅም ቢወራ ፡
ከሰማያት ወርዶ ሆነ ከኛ ጋራ (2)።
አዝማች - -
ስራውን እናድንቅ እንዲህ ለወደደን ፡
ከማይልቀው ፍቅሩ በረከት ላደለን።
ለማይነገረው ለአምላክ ስጦታ ፡
ውዳሴን እናቅርብ እንዘምር በልልታ (2)።
Century
Language