ቢሆንም ከጊዜ በኋላ “ክርስቲያን” የሚለው ቃል ትክክለኛ ትርጉሙ አጥቶ የክርስቶስ ተከታይ ለሆነውም ፡ ሳይሆንም ግብረ ገባዊ በሆነ መንገድ ለሚመላለስ ማንኛውንም ሃይማኖተኛ የሚሰጥ ስም ሆኖ እናገኘዋለን። ብዙ ሰዎች በ ኢየሱስ ክርስቶስ ባያምኑም አንኳን ወደ ቤተ ክርስቲያን በመመላለሳቸው ወይንም “ክርስቲያን” በሆነ አገር በመኖራቸው ብቻ ራሳቸውን ክርስቲያን ብለው ይሰይማሉ። ቢሆንም ግን ወደ ቤተ ክርስቲያን መመላለስ፣ ካነተ በታች የሆኑትን መርዳትና ጥሩ ሰው ሆኖ መገኘት ብቻ በራሱ ክርስቲያን አያደርግህም። የቤተ ክርስቲያን አባል መሆን፣ ጉባኤ መከታተልና የቤተ ክርስቲያንን ሥራ መሥራት ብቻ ክርስቲያን አያደርግህም።
መጽሐፍ ቅዱስ እንደሚያስተምረን የምንሠራው በጎ ሥራ ብቻውን በእግዚአብሔር ዘንድ ተቀባይነትን አያስገኝልንም። ቲቶ ፫፥፭ እነዲህ ይለናል፤ “ስላደረግነው የጽድቅ ሥራ ሳይሆን፣ ከምሕረቱ የተነሣ አዳነን። ያዳነንም ዳግም ልደት በሆነው መታጠብና በመንፈስ ቅዱስ መታደስ ነው።” ስለዚህ፣ ክርስቲያን ማለት በእግዚአብሔር እንደገና የተወለደና (ዮሐንስ ፫፥፫፤ ዮሐንስ ፫፥፯፤ ፩ኛ ጴጥሮስ ፩፥ ፳፫) እምነቱንም በክርስቶስ ያደረገ ሰው ነው። ኤፌሶን ፪፥፰ እነደሚለን፣ “በእምነት፣ በጸጋ ድናችኋልና፤ ይህም የእግዚአብሔር ስጦታ ነው እንጂ ከ እናንተ አይደለም።” እውነተኛው ክርስቲያን ለኀጢአቱ ንስሓ የገባና በኢየሱስ ክርስቶስ ብቻ ያመነ ነው። እውነተኛ ክርስቲያኖች እምነታቸው ሃይማኖትን፣ ግብረ ገባዊ ሕጎችንና “አድርግ አታድርግ” ዝርዝሮችን ላይ አይደለም።
እውነተኛ ክርስቲያን እምነቱ በክርስቶስ ያደረገ፣ ክርስቶስ መስቀል ላይ የሞተው ለኀጢአታችን ሲል እነደሆነና በሦስተኛውም ቀን ከሙታን ተነስቶ ሞት ላይ አቸናፊነቱን ያረጋገጠው በሱ ለሚያምኑ ዘለዓለማዊ ሕይወትን ለመስጠት መሆኑን ያመነ ማለት ነው። ዮሐንስ ፩፥፲፪ እንዲህ ይለናል፤ “ለተቀበሉትና በስሙ ላመኑት ሁሉ ግን የእግዚአብሔር ልጆች የመሆን መብት ተሰጣቸው።” እውነተኛው ክርስቲያን የእግዚአብሔር ልጅ ነው፤ እንዲሁም የእግዚአብሔር ቤተሰብ አባልና በክርሰቶስ አዲስ ሕይወት የተሰጠው ነው። የእውነተኛ ክርስቲያን መለያ ለሌሎች በሚያሳየው ፍቅርና ለእግዚአብሔር ቃል በሚያሳየው መታዘዝ ነው (፩ኛ ዮሐንስ ፪፥፬፤ ፩ኛ ዮሐንስ ፪፥፲)።
Language