First century from 1 to 100 AD.
ሐዋርያው ዮሐንስ በአራቱም ወንጌላት ውስጥ ከ12ቱ ሐዋርያት ቀደምት ከተባሉት ከሶስቱ መካከል አንዱ እንደነበረ ይታወቃል። እሱና ወንድሙ ያዕቆብ ሁለቱም የገሊላ ዓሣ አጥማጆች የነበሩ ሲሆኑ ፡ ኢየሱስ “የነጎድጓድ ልጆች” እያለ ይጠራቸው ነበር። ዮሐንስ ለኢየሱስ ክርስቶስ ከመቅረቡ የተነሳ ፡ ጌታችን ለፈጸማቸው ብዙ ተአምራት የአይን ምስክር ነበር። በተለይም ጌታችን በደብረ ታቦር ተራራ አምላክነቱን ያሳየበት ተአምራዊ ለውጥን ካዩት ከሶስቱ ሃዋርያት አንዱ ዮሐንስ ነበር። በጌተሰማኒ በአትክልቱ ስፍራ ክርስቶስ የተሰቃየውን ስቃይ ጨምሮ፡ እስከ ስቅለተ ሞቱ ድረስ ዮሐንስ አብሮት ነበረ።
- Read more about ሐዋርያው ዩሐንስ
- Log in or register to post comments