ፊልጶስ ቂሣርያ

Caesarea Philippi (ፊልጶስ ቂሣርያ) Source of Water

ከገሊላ ባሕር በስተ ሰሜን 40 ኪሎ ሜትር እንዲሁም ከሄርሞን ተራራ ግርጌ የምትገኘው ፊልጶስ ቂሣርያ የዮርዳኖስ ወንዝን ከሚመግቡት ትልልቅ ምንጮች መካከል የአንዱ መፍለቂያ ስፍራ ናት። ይህ የተትረፈረፈ የውኃ አቅርቦት አካባቢው ለምና ለሃይማኖታዊ አምልኮ ማራኪ እንዲሆን አድርጎታል። በግሪካውያንና በሮማውያን ዘመን በዚህች ከተማ በርካታ የጣአኦታት ቤተ መቅደሶች ተገንብተው ነበር።

ከዚህ በታች ባለው ካርታ ላይ እንደሚታየው ፊልጶስ ቂሣርያ ከገሊላ ባህር በስተሰሜን ምስራቅ በሃምሳ ኪሎሜትር ርቀት የምትገኝ ከተማ ነበረች። በሄርሞን ተራራ ስር የምትገኝ ከተማ ስትሆን ከተራራው ስር የሚፈልቁ ምንጮች ወደ ዮርዳኖስ ወንዝ ይፈሳሉ።

Caesarea Philippi Map (ፊልጶስ ቂሣርያ ካርታ)

በክርስትና እምነት ፊልጶስ ቂሣርያ ትልቅ ቦታ ያላት ናት። ጌታችን መድሃኒታችን ኢየሱስ ክርስቶስ የህያው እግዚአብሔር ልጅ መሆኑን ሃዋርያው ቅዱስ ጴጥሮስ የመሰከረባት ቦታ በምሆኗ በደስታ እናስታውሳታለን።

የማቴዎስ ወንጌል - ምዕራፍ 16

13 ኢየሱስም ወደ ፊልጶስ ቂሣርያ አገር በደረሰ ጊዜ ደቀ መዛሙርቱን። ሰዎች የሰውን ልጅ ማን እንደ ሆነ ይሉታል? ብሎ ጠየቀ።
14 እነርሱም። አንዳንዱ መጥምቁ ዮሐንስ፥ ሌሎችም ኤልያስ፥ ሌሎችም ኤርምያስ ወይም ከነቢያት አንዱ ነው ይላሉ አሉት።
15 እርሱም። እናንተስ እኔን ማን እንደ ሆንሁ ትላላችሁ? አላቸው።
16 ስምዖን ጴጥሮስም መልሶ። አንተ ክርስቶስ የሕያው እግዚአብሔር ልጅ ነህ አለ።
17 ኢየሱስም መልሶ እንዲህ አለው። የዮና ልጅ ስምዖን ሆይ፥ በሰማያት ያለው አባቴ እንጂ ሥጋና ደም ይህን አልገለጠልህምና ብፁዕ ነህ።

ከዚህ በታች ያለው ቪዲዮ ተጨማሪ ግንዛቤን ይሰጠናል።

Video
Century