የሚጠብቀኝ አይተኛም

ዘማሪ ይልማ ሀይሉ

የሚጠብቀኝ አይተኛም

አዝማች
የሚጠብቀኝ አይተኛም (2)
አያንቀላፋም።

ቤት ባይኖረኝም ደጅ ባድርም
ቀን እና ሌሊት ከኔ አይረቅም
ድምፀ አራዊት የሌሊት ግርማ
ወደ እኔ አይቀርቡም ድምፅህ ሲሰማ

አዝማች
የሚጠብቀኝ አይተኛም (2)
አያንቀላፋም።

መሰናክልን ለእግሮጬ አይሰጥም
ይሰውረኛል በቀኙ ሰላም
ፀሀይም በቀን አይተኩሰኝም
የአጋንንትም ሀይል አያስፈራኝም

አዝማች
የሚጠብቀኝ አይተኛም (2)
አያንቀላፋም።

ነብሴን ጠበቃት ከጠላት ወጥመድ
ጌታዬ መራኝ በፅድቅ መንገድ
መውጣት መግባቴን እየጠበቀ
ለዚህ አበቃኝ እሱ በአወቀ

አዝማች
የሚጠብቀኝ አይተኛም (2)
አያንቀላፋም።

የሰማዩን ጥል እታገሳለው
ሰው ከጨከነ ምን እሆናለው
ሌሊት በድብቅ ለሚጎበኙኝ
ለፃድቃኑ ግን አምላክ ይስጥልኝ

አዝማች
የሚጠብቀኝ አይተኛም (2)
አያንቀላፋም።

እንቅልፌን ባርኮ የሰጠኝ ጌታ
በአለም ሀሳብ ሳልንገላታ
የ እለት ምግቤንም ላልነሳኝ ፍፁም
ምስጋና ላቅርብ እስከዘላለም

አዝማች
የሚጠብቀኝ አይተኛም (2)
አያንቀላፋም።