Fourth Century from 301 - 400 AD
የኒቂያ ጉባኤ የተካሄደው ከክርስቶስ ልደት በኋላ በሮማ ንጉሠ ነገሥት ቄሣር በፍላቪየስ ቆስጠንጢኖስ ትእዛዝ በ 325 ዓመተ ምህረት ነበር። ኒቂያ የምትገኘው ከቁስጥንጥንያ በስተምሥራቅ በምትገኘው በትንሿ እስያ ነበር ። በኒቂያ ጉባኤ ላይ አፄ ቆስጠንጢኖስ የክርስቶስን አምላክነት በተመለከተ በቤተ ክርስቲያኒቱ ውስጥ ያለውን ግራ መጋባት፣ ውዝግብና አለመስማማት ለማስወገድ በሚል ዓላማ 318 የቤተ ክርስቲያን ሊቃውንት ጳጳሳትንና ሌሎች መሪዎች የተገኙበትን ጉባኤ መርተዋል። የኒቂያ ጉባኤ የኢየሱስ ክርስቶስን አምላክነት እና ዘላለማዊነት በከፍተኛ ሁኔታ አረጋግጦ በአብ እና በወልድ መካከል ያለውን መተካከል ተቀብሎ አጽንቶታል።
- Read more about የኒቂያ የእምነት አንቀጽ
- Log in or register to post comments