መቄዶኒያ

Phillipi (ፊልጵስዮስ)

መቄዶንያ በአዲስ ኪዳን ዘመን ከግሪክ በስተሰሜን የምትገኝ የሮማ ግዛት ነበረች። ሃዋርያው ቅዱስ ጳውሎስ በሁለተኛው የሚሽን ጉዞው ላይ ሳለ ወደ መቄዶንያ ሄዶ እንዲያስተምር ራእይ አየ። ጳውሎስ በወንጌላዊነቱ የሚሽን ሥራ ላይ ካተኮረባቸው አራት ዋና ዋና አካባቢዎች አንዷ ይህቺው በግሪክ ሰሜናዊ ክፍል የምትገኘው መቄዶንያ ነበረች ። 

የሐዋርያት ሥራ - ምዕራፍ 16፡ 8-10
በሚስያም አጠገብ አልፈው ወደ ጢሮአዳ ወረዱ። ራእይም ለጳውሎስ በሌሊት ታየው፤ አንድ የመቄዶንያ ሰው። ወደ መቄዶንያ ተሻገርና እርዳን እያለ ቆሞ ሲለምነው ነበር። 10 ራእዩንም ካየ በኋላ ወዲያው ወደ መቄዶንያ ልንወጣ ፈለግን፥ ወንጌልን እንሰብክላቸው ዘንድ እግዚአብሔር እንደ ጠራን መስሎናልና።

ሃዋርያው ቅዱስ ጳውሎስ ለቆሮንቶስ ሰዎች በላከው ሁለተኛው መልክቱ ላይ ወደ መቄዶንያ ሄዶ ወንጌልን መስበኩ ትልቅ በረከት እንደነበረ እንረዳለን።

2ኛ ወደ ቆሮንቶስ ሰዎች -ምዕራፍ 8

1 ወንድሞች ሆይ፥ ለመቄዶንያ አብያተ ክርስቲያናት የተሰጠውን የእግዚአብሔርን ጸጋ እናስታውቃችኋለን፤ በብዙ መከራ ተፈትነው ሳሉ የደስታቸው ብዛትና የድህነታቸው ጥልቅነት የልግስናቸውን ባለ ጠግነት አብዝቶአል፤ እንደ ዓቅማቸው መጠን ከዓቅማቸውም የሚያልፍ እንኳ ወደው እንደ ሰጡ እመሰክርላቸዋለሁና።
ለቅዱሳን በሆነው አገልግሎት እንዲተባበሩ ይህን ቸርነት በብዙ ልመና ከእኛ ይለምኑ ነበር፥ አስቀድመውም በእግዚአብሔር ፈቃድ ራሳቸውን ለጌታ ለእኛም ሰጡ እንጂ እንዳሰብን አይደለም።

ከዚህ በታች ያለው ቪዲዮ ሃዋርያው ቅዱስ ጳውሎስ መቄዶንያን ምሳሌ በመጥቀስ ስለ ምጽዋትና ስለለጋስነት ያስተማረውን መልእክት የያዘ ነው።አይታችሁ አስተያየታችሁንና ግንዛቤአችሁን እንድትሰጡ ፡ ጥያቄም ካላችሁ እንድትጠይቁ ተጋብዛችኋል።

Video
Language