ከኃጢአተኛው ድንኳን

ዘማሪ ዲ/ን አቤል መክብብ

አዝማች

ከሃጢያተኛው ድንኳን ቅዱሱ ቆመሃል
ልጄ የት ነው ብለህ እኔን ፈልገሃል
አንተ ስላለኽኝ ቀልሏል መከራዬ
ለኔ ያደረግከው ብዙ ነው ጌታዬ

እንኳንስ አርገኽኝ ጌታዬ ሙሉ ሰው
እንዲሁም ይሄን ነው ልቤ የሚናፍቀው
የዘመናት ሸክም ቀረ ጉስቁልና
የጠፋውን ድሪም አግኝተሃልና

አዝማች---

ባገኘኽኝ ግዜ ሸፍናኝ በለሷ
ከፊትህ ያነበብኩት ፈጽሞ አይረሳ
ከዚህ የበለጠ ታያለህ የምትለኝ
አይንህ ይናገራል እንደማትረሳኝ

አዝማች---

ምን አለኝ ብለህ ነው ደጃፌን የምትመታ
እኔ ደካማ ነኝ አንተ ቅዱስ ጌታ
ከእንግዲህ አላርስም ምንጣፌን በዕምባ
መንጦላዕቴን ከፍተህ በምህረትህ ግባ

አዝማች---

እኔ እኮ አውቅሃለሁ ሁሉን ስታፈቅር
የአናብስቱን ጉድጓድ የሞት አዋጅ ስትሽር
እንዲህ እያለ ነው የሚቀኘው ውስጤ
ኢየሱስ ክርስቶስ ምግቤና መጠጤ

Century
Language