ዮሴፍ በቀለ
አዝማች
እስኪ መስቀልህ ስር ሸክሜን ልጣለው (2x) አዎ
ማረፊያዬ ኢየሱስ ሰላሜ በአንተ ነው እረፍቴ በአንተ ነው አዎ
ሁሉ ያለቀበትን መስቀልህን እያየሁ (2x) ኦሆ
ያኔ መከራዬን ችግሬን እረሳለሁ ጭንቀቴን እረሳለሁ አዎ
በቀራኒዮ ላይ ስለእኔ ተሰቅለህ (2x) ኦሆ
አንተ ከእኔ ፈንታ እርጉም ሰው ተብለህ (2x) አዎ
ተፈጸመ ብለህ ሁሉንም ጨረስከው (2x) ኦሆ
ለዘለዓለሙ መርገሜን ወሰድከው እዳዬን ከፈልከው አዎ
መራራውን ጽዋ ጠጣህ በእኔ ፈንታ
የታሰርኩበትን ሰንሰለት እየፈታህ
መስቀልህ ስር አለሁ ጥያቄዬን ይዤ
ከላዬ ውሰደው ኢየሱስ ወዳጄ
አዝ፦ እስኪ መስቀልህ ስር ሸክሜን ልጣለው (2x) አዎ
ማረፊያዬ ኢየሱስ ሰላሜ በአንተ ነው እረፍቴ በአንተ ነው አዎ
ሁሉ ያለቀበትን መስቀልህን እያየሁ (2x) ኦሆ
ያኔ መከራዬን ችግሬን እረሳለሁ ጭንቀቴን እረሳለሁ አዎ
ሸክም ሲያንገላታኝ ቀንበር ሲከብድብኝ (2x) ኦሆ
ጨለማው በርትቶ መሄጃው ሲጠፋኝ (2x) አዎ
ቀና ብዬ ሳይህ ስጠራህ ጌታዬ (2x) ኦሆ
ፈጥነህ ድረስና ስበርው ከላዬ ቀንበሩን ከላዬ አዎ
ከእናት ከአባት በላይ ቀርበህ ምትረዳኝ
ሚስጢሬን ተካፋይ ማን እንዳንተ ጌታ
ገበናዬን ሸፋኝ ሚስጢረኛዬ ነህ
ከማንም ከምንም ትበልጥብኛለህ
ከታላቁ ስፍራ ከእዛ የወረድከው
ፍቅር ያስገደደህ ለእኔ ነው ለእኔ ነው
ችግሬን ሚረዳኝ እንዳንተ የለምና
ሁሉን ነግርሃለሁ ፊትህን እደፋና
Century