በርተሚዮስ ነኝ

Bertemious the blind (በርተሚዮስ ነኝ አይነ ስውር ምስኪን)
ሊቀ መዘምራን ይልማ ኃይሉ

አዝማች

በርተሚዮስ ነኝ አይነ ስውር ምስኪን።

ከሩቅ የሰማሁት የጌታዬ ድምጹን።

ከብዙ ሁካታ ጉርምርምታ መሃል የክርስቶስ ድምጹ በግልጽ ይሰማኛል።

የልቦናዬ አይን ፈጽሞ ታውሯል፡ አይኔን ፈውስልኝ በርተሚዮስ ይላል።

አብዝቼ እጮሃለው ጌታ ማረኝ ብዬ ፡ በውስጤ እየታየኝ ሲምረኝ ጌታዬ።

አንተን አይሰማህም ይሉኛል ብዙዎች ፡ በሃጢያት ሰንሰለት ታስረሃል አቅተዎች፡

ስለዚህ አትልፋ ፡ ሲኦልን ጠብቃት። እንደዚህ ቢሉኝም እጮሃለሁ ሳልታክት። 

   አዝማች

   በርተሚዮስ ነኝ አይነ ስውር ምስኪን።

   ከሩቅ የሰማሁት የጌታዬ ድምጹን። 

   ከብዙ ሁካታ ጉርምርምታ መሃል የክርስቶስ ድምጹ በግልጽ ይሰማኛል። 

 

የከበበውን ሰው ገለል በሉ እያለ ፡ በደሌን በደሙ ዋጋ እየከፈለ ፡

ስለኔ የሞተው እየሱስ ይመጣል ፡ የልቦናዬን አይን ገልጾ ያሳየኛል።

አብዝቼ እጮሃለው ጌታ ማረኝ ብዬ ፡ በግልጽ እየታየኝ ሲምረኝ ጌታዬ።

በውስጤ በደልስ ሕይወቴ ዝላለች ፡ ባምላኬ ቸርነት ሕይወት ካላገኘች።  

 

   አዝማች

   በርተሚዮስ ነኝ አይነ ስውር ምስኪን።

   ከሩቅ የሰማሁት የጌታዬ ድምጹን። 

   ከብዙ ሁካታ ጉርምርምታ መሃል የክርስቶስ ድምጹ በግልጽ ይሰማኛል። 

 

Century
Language