በሐዋርያት ሥራ መጽሐፍ በጉልህ እንደተቀመጠው አንጾኪያ ለክርስትና እምነት መስፋፋት ትልቅ ሚና ተጫውታለች ። ከተማዋ ከእየሩሳሌም ተሰደው ለወጡ ክርስትናን ለተቀበሉ አይሁዳውያን መጠጊያ ስፍራ ነበረች። ከዚህ በታች ባለው ምስል ላይ እንደምታዩት የክርስቶስ ተከታዮች ወደ ፊንቄ፤ ወደ ቆጵሮስ በተለይም ደግሞ ወደ አንጾኪያ ተሰደው ነበር።
የሐዋርያት ሥራ - ምዕራፍ 11 ቁጥር 19 - 20
19 በእስጢፋኖስም ላይ በተደረገው መከራ የተበተኑት እስከ ፊንቄ እስከ ቆጵሮስም እስከ አንጾኪያም ድረስ ዞሩ፥ ቃሉንም ለአይሁድ ብቻ እንጂ ለአንድ ስንኳ አይናገሩም ነበር። 20 ከእነርሱ ግን የቆጵሮስና የቀሬና ሰዎች የነበሩት አንዳንዶቹ ወደ አንጾኪያ መጥተው የጌታን የኢየሱስን ወንጌል እየሰበኩ ለግሪክ ሰዎች ተናገሩ።
ከላይ የእግዚአብሔር ቃል በሆነው መጽሃፍ እንደተገለጸው አንጾኪያ ከተልያየ አካባቢ በመጡ አማኞች የኢየሱስ ወንጌል የሚሰበክባት ከተማ እንደነበረች እንገነዘባለን። አማኞቹ ከምን ያህል ርቀት ይመጡ እንደነበረ ከዚህ በታች ባለው ካርታ ልንገነዘብ እንችላለን።
ከሁሉም በላይ አንጾኪያን እንዳትዘነጋ የሚያደርጋት ደቀ መዛሙርት ለመጀመሪያ ግዜ ክርስትያን ተብለው የተጠሩት በአንጾኪያ በመሆኑ ነው።
የሐዋርያት ሥራ - ምዕራፍ 11 ቁጥር 25 - 26
25 በርናባስም ሳውልን ሊፈልግ ወደ ጠርሴስ መጣ፤
26 ባገኘውም ጊዜ ወደ አንጾኪያ አመጣው። በቤተ ክርስቲያንም አንድ ዓመት ሙሉ ተሰበሰቡ፥ ብዙ ሕዝብንም አስተማሩ፤ ደቀ መዛሙርትም መጀመሪያ በአንጾኪያ ክርስቲያን ተባሉ።
ይህ እንግዲህ ለክርስትና እምነት ታሪክ ትልቅ ቦታ አለው። ይህ ብቻ አይደለም። ሃዋርያው ቅዱስ ጳውሎስና በርናባስ እየዞሩ በአህዛብ ምድር ወንጌልን እንዲሰብኩ ሃላፊነት ተቀብለው የተሰማሩት ከዚችው ከአንጾኪያ ነበር።
የሐዋርያት ሥራ - ምዕራፍ 13 ቁጥር 1 - 4
1 አንጾኪያም ባለችው ቤተ ክርስቲያን ነቢያትና መምህራን ነበሩ፤ እነርሱም በርናባስ፥ ኔጌር የተባለው ስምዖንም፥ የቀሬናው ሉክዮስም፥ የአራተኛው ክፍል ገዥ የሄሮድስም ባለምዋል ምናሔ፥ ሳውልም ነበሩ። 2 እነዚህም ጌታን ሲያመልኩና ሲጦሙ መንፈስ ቅዱስ። በርናባስንና ሳውልን ለጠራኋቸው ሥራ ለዩልኝ አለ። 3 በዚያን ጊዜም ከጦሙ ከጸለዩም እጃቸውንም ከጫኑ በኋላ አሰናበቷቸው። 4 እነርሱም በመንፈስ ቅዱስ ተልከው ወደ ሴሌውቅያ ወረዱ፤ ከዚያም በመርከብ ወደ ቆጵሮስ ሄዱ።
Video
Language
Sources